ከየትም ቦታ በማንኛዉም ሰዓት ብቃት ባላቸው አስጠኚዎች ይማሩ
ብቃት ካላቸው አስጠኚዎች ጋር በመስመር ላይ ይገናኙ። ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ለአጠቃቀም ምቹ እንዲሁም ለማንኛዉም የጊዜ ፕሮግራምዎ የሚስማማ ነው። ለኢትዮጵያ ተማሪዎች እና በዓለም ዙሪያ ላሉ ቤተሰቦች ተስማሚ ነው።
ማንን እንረዳለን
ለሁሉም ሰው፣ ለሁሉም ቦታ ጥራት ያለው ትምህርት
ለኢትዮጵያ ተማሪዎች
ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል፣ የኢትዮጵያ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርትን ለሚከተሉ
በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች
ከኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጋር ያላቸውን ትስስር ለማስጠበቅ
ዓለም አቀፍ ተማሪዎች
አይጂሲኤስሲኢ፣ ጂሲኤስሲኢ፣ አይቢ፣ አሜሪካዊ እንዲሁም ሌሎች ሥርዓተ ትምህርቶችን የሚከተሉ
ትምህርት ቤቶች እና ድርጅቶች
ከእኛ ጋር ተባብረው ይስሩ
ወላጆች ለምን እኛን ይመርጣሉ
ለተለመዱ ችግሮች ቀላል መፍትሄዎች
የልጅዎ ደህንነት
ስለ ልጅዎ ደህንነት ማንኛውም ስጋት ቢኖር፣ ሁሉም የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ይቀዳሉ እንዲሁም ለኋላ ለግምገማ ይቀመጣሉ።
ግላዊነት እና ደህንነት
እንግዳ ወደ ቤትዎ አይመጣም። ሁሉም ነገር ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በመስመር ላይ ይከናወናል።
በማንኛውም ሰዓት ይገኛል
ጠዋት፣ ከሰዓት በኋላ፣ ማታ ወይም ሌሊት ላይ ቀጠሮ መያዝ ይቻላል። እኛ ሁልጊዜ ክፍት ነን።
ብቁ አስጠኚዎቸ
ሁሉም አስተማሪዎች በጥንቃቄ ተመርጠው ሥልጠና ይሰጣቸዋል። ከኢትዮጵያ ታዋቂ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ናቸው።
ተመጣጣኝ ዋጋ
ከተለምዶ ቤት ለቤት አስጠኚዎች በጣም ርካሽ ነው። የቡድን ክፍለ ጊዜዎች የበለጠ ይቀንሳሉ።
ነጻ የወላጆች ሥልጠና
ልጅዎ በቤት ውስጥ በተሻለ መንገድ እንዲማር እንዴት መርዳት እንደሚችሉ እናሠለጥንዎታለን።
ቀላል ተመጣጣኝ ዋጋ
ለእርስዎ የሚስማማውን እቅድ ይምረጡ
የግል ጥናት
አንድ ለአንድ-
የሰዓት ተመን ከ350 ብር ይጀምራል
-
ተለዋዋጭ የጊዜ ፕሮግራም – በማንኛውም ጊዜ ቀጠሮ ይያዙ
-
በመጀመሪያው ሳምንት ነጻ የሙከራ ክፍለ ጊዜ
-
እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ይቀዳል እንዲሁም ለሦስት ወራት ይቀመጣል (የግል ማስፈንጠሪያ)
-
አጫጭር ማስታወሻዎች፣ ጥያቄዎች እና የልምምድ ፈተናዎች
-
ወላጆች በተማሪው ዳሽቦርድ በኩል እድገቱን ይከታተላሉ
-
ነጻ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ባንክ እንዲሁም ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ያነጣጠረ ዝግጅት
-
በቀጠሮ መያዣ ገጽ ላይ የሚመርጡትን አስጠኚ ይምረጡ
ስፓርክ ትሪዮ
በአንድ አስተማሪ ሦስት ተማሪዎች-
ወርሃዊ ክፍያ በአንድ ተማሪ 2,300 ብር
-
ሦስቱ መቀመጫዎች ሲሞሉ ክፍለ ጊዜዎች ይጀምራሉ
-
በመጀመሪያው ሳምንት ነጻ የሙከራ ክፍለ ጊዜ
-
እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ይቀዳል እንዲሁም ለሦስት ወራት ይቀመጣል (የግል ማስፈንጠሪያ)
-
አጫጭር ማስታወሻዎች፣ ጥያቄዎች እና የልምምድ ፈተናዎች
-
ወላጆች በተማሪው ዳሽቦርድ በኩል እድገቱን ይከታተላሉ
-
ነጻ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ባንክ እንዲሁም ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ያነጣጠረ ዝግጅት
-
በቀጠሮ መያዣ ገጽ ላይ የሚመርጡትን አስጠኚ ይምረጡ
ስፓርክ ኩዊንት
በአንድ አስተማሪ አምስት ተማሪዎች-
ወርሃዊ ክፍያ በአንድ ተማሪ 1,800 ብር
-
አምስቱ መቀመጫዎች ሲሞሉ ክፍለ ጊዜዎች ይጀምራሉ
-
በመጀመሪያው ሳምንት ነጻ የሙከራ ክፍለ ጊዜ
-
እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ይቀዳል እንዲሁም ለሦስት ወራት ይቀመጣል (የግል ማስፈንጠሪያ)
-
አጫጭር ማስታወሻዎች፣ ጥያቄዎች እና የልምምድ ፈተናዎች
-
ወላጆች በተማሪው ዳሽቦርድ በኩል እድገቱን ይከታተላሉ
-
ነጻ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ባንክ እንዲሁም ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ያነጣጠረ ዝግጅት
-
በቀጠሮ መያዣ ገጽ ላይ የሚመርጡትን አስጠኚ ይምረጡ
እንዴት መጀመር ይቻላል
በአራት ቀላል ደረጃዎች ይጀምሩ – ከአምስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ዉስጥ።
መለያ ይፍጠሩ
ከሁለት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ በነጻ ይመዝገቡ። ለመጀመሪያ የሙከራ ክፍለ ጊዜዎ ምንም ክፍያ አይጠየቅም።
አስጠኚ ይምረጡ
አስጠኚዎቻችንን ይመልከቱ፣ በትምህርት ዓይነት፣ ሥርዓተ ትምህርት፣ የሚገኙበትን ጊዜ እና ደረጃቸውን ያስተውሉ።
ቀጠሮ ይያዙ
ለእርስዎ የሚስማማ ጊዜ ይምረጡ። መድረኩ ሁልጊዜም ክፍት ነወ። የግል ወይም የቡድን ክፍለ ጊዜዎችን ይምረጡ።
መማር ይጀምሩ
በአንድ ጠቅታ ክፍለ ጊዜዎን ይቀላቀሉ። ማውረድ አያስፈልግም ። በይነመረብ ባለው ማንኛውም መሣሪያ ላይ ይሠራል።
ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች
ስለ ላይትአፕ አገልግሎቶች ማወቅ የሚፈልጉትን በተብራራ መልኩ አቀርበናል
ላይትአፕ በመስመር ላይ በሚደረጉ ክፍለ ጊዜዎች ወቅት የልጄን ደህንነት የሚያረጋግጥልኝ እንዴት ነው?
ሁሉም የአስጠኚ ክፍለ ጊዜዎች ይመዘገባሉ እንዲሁም ወላጆች እንዲገመግሙ በደህንነት ይቀመጣሉ። የእኛ መድረክ ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ምህዳር ይጠብቃል፤ አስተማሪዎችም በጥብቅ መመሪያዎች መሠረት ይሠራሉ። ወላጆች ክፍለ ጊዜዎችን መከታተል እንዲሁም ሙሉ ደህንነትን ለማረጋገጥ ቅጂዎችን በማንኛውም ጊዜ መገምገም ይችላሉ።
ለመጀመር ምን ዓይነት መሣሪያዎች ያስፈልጉኛል?
ዲጂታል የመጻፊያ መሣሪያ (ከስታይለስ ጋር ታብሌት፣ ከስታይለስ ጋር ላፕቶፕ፣ ወይም ዲጂታል ብዕር ታብሌት) እንዲሁም የተረጋጋ የበይነመረብ ግንኙነት (ቢያንስ 2 ሜባኤስ) ያስፈልግዎታል። ዲጂታል የመጻፊያ መሣሪያ ከሌለዎት፣ ላይትአፕ ከማንኛውም ኮምፒውተር ጋር የሚስማማ ዲጂታል ብዕር ታብሌት በምክንያታዊ ዋጋ ማቅረብ ይችላል።
በእውነት በ24/7 አስተማሪዎችን ማግኘት እችላለሁን?
አዎን። የእኛ መድረክ በ24 ሰዓት፣ በ7 ቀን፣ በ365 ቀናት ውስጥ ይንቀሳቀሳል። ለእርስዎ የሚስማማውን ጊዜ በቀላሉ ይምረጡና በዚያ ጊዜ የሚገኙ አስተማሪዎችን ይያዙ። ይህ ተለዋዋጭነት በተለይ በተለያዩ የሰዓት ሰቆች ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች ወይም ሥራ ለሚበዛባቸው ተማሪዎች ጠቃሚ ነው።
የአስጠኚ ክፍያ ምን ያህል ነው?
ከባህላዊ የቤት ውስጥ አስጠኚነት በእጅጉ ያነሱ ተመጣጣኝ ዋጋዎችን እናቀርባለን። ዋጋው እንደ ክፍለ ጊዜው አይነት ይለያያል፦ የግል፣ ትናንሽ ቡድኖች (2-3 ተማሪዎች)፣ ወይም ትልልቅ ቡድኖች (እስከ 5 ተማሪዎች)። የቡድን ክፍለ ጊዜዎች ጥራት ያለው ትምህርት ሲጠበቅ የበለጠ ቁጠባ ያስገኛሉ።
አስተማሪዎችዎ ምን ሥርዓተ ትምህርቶችን ይሸፍናሉ?
አስተማሪዎቻችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥርዓተ ትምህርት (ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል)፣ ኢንተርናሽናል ባካላሪየት (አይቢ)፣ ካምብሪጅ አይጂሲኤስሲኢ/ኤ-ሌቨል፣ አሜሪካዊ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ የፈተና ዝግጅት (ኤስኤቲ ወዘተ.) ለማስተማር ብቁ ናቸው። በተጨማሪም ለዲያስፖራ ቤተሰቦች የአማርኛ ቋንቋ እና የኢትዮጵያ ባህል ፕሮግራሞችን እናቀርባለን።
አስተማሪዎች እንዴት ይመረጣሉ እና ብቃታቸው ምን ይመስላል?
ሁሉም አስተማሪዎች ጥብቅ የማጣሪያ ሂደት ውስጥ ያልፋሉ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ታዋቂ ትምህርት ቤቶች ይመረጣሉ። በመስመር ላይ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴ እና በትምህርት ዘርፍ ልዩ ሥልጠና በእኛ ወጪ ይሰጣቸዋል። እያንዳንዱ አስተማሪ ለአካዳሚክ ልቀት እና ለማስተማር ችሎታ ያለንን ከፍተኛ መስፈርት እንዲያሟሉ እናረጋግጣለን።
ልጄ ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ አንድ አስተማሪ ሊኖረው ይችላልን?
አዎን። ከልጅዎ ጋር በጥሩ ሁኔታ የሚሠራ አስተማሪ ካገኙ በኋላ፣ ወጥነትን ለመጠበቅ እና ጠንካራ የትምህርት ግንኙነት ለመገንባት ከዚያው አስተማሪ ጋር ተደጋጋሚ ቀጠሮዎችን መያዝ ይችላሉ።
በአንድ ክፍለ ጊዜ ካልረካሁ ምን ማድረግ አለብኝ?
በአንድ ክፍለ ጊዜ ካልተደሰቱ፣ እባክዎን የድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ። ስጋቶችን ለመፍታት፣ አስፈላጊ ከሆነ ከሌላ አስተማሪ ጋር ለማዛመድ፣ ወይም ተገቢ መፍትሄዎችን ለማቅረብ እንሠራለን።
ነጻ የሙከራ ክፍለ ጊዜ ታቀርባላችሁን?
አዎን። መድረካችንን እና የማስተማር ጥራታችንን ከመግዛትዎ በፊት እንዲለማመዱ ነጻ የሙከራ ክፍለ ጊዜ እናቀርባለን። ሙከራዎን ለመጀመር ምንም ክፍያ አያስፈልግም።
የመስመር ላይ አስጠኚነት ከአካላዊ አስጠኚነት ጋር ሲነጻጸር እንዴት ነው?
የመስመር ላይ አስጠኚነት ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣል፦ የመጓጓዣ ጊዜ አያስፈልግም፣ ሰፋ ያለ ልዩ ባለሙያ አስተማሪዎችን ማግኘት፣ 24/7 ተገኝነት፣ ለግምገማ የሚቀመጡ ቅጂዎች፣ ዝቅተኛ ወጪ እና የተሻሻለ ደህንነት። የእኛ መድረክ የመስመር ላይ ትምህርትን ከባህላዊ አስጠኚነት ጋር እኩል ወይም ከዚያ በላይ ውጤታማ የሚያደርጉ በይነተግባባዊ መሣሪያዎችን ያቀርባል።
ወላጆች ክፍለ ጊዜዎችን መከታተል ወይም መሳተፍ ይችላሉን?
በእርግጠኝነት። ወላጆች በክፍለ ጊዜዎች ላይ እንዲገኙ እንፈቅዳለን፣ እንዲሁም ሁሉም ክፍለ ጊዜዎች ለኋላ ግምገማ ይመዘገባሉ። በተጨማሪም ወላጆች የልጃቸውን የትምህርት ጉዞ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲደግፉ ልዩ ሥልጠና እንሰጣለን።
ምን ያህል የኢንተርኔት ፍጥነት ያስፈልገኛል?
ቢያንስ 2 ሜባኤስ ያስፈልጋል። ባለገመድ ወይም የተረጋጋ ገመድ አልባ ግንኙነት እንዲጠቀሙ እንመክራለን። የሞባይል ሆትስፖት ሊሠሩ ቢችሉም፣ ያልተቋረጠ ትምህርት ለማረጋገጥ ለአስጠኚ ክፍለ ጊዜው ብቻ የተወሰነ መሆን አለበት (ስልክ አይደውሉ)።
በላይትአፕ አስተማሪ መሆን የምችለው እንዴት ነው?
ክፍት የሥራ መደቦችን ለማየት እና ለማመልከት እባክዎን ‘ከእኛ ጋር ይስሩ’ የሚለውን ገጻችንን ይጎብኙ። የማስተማር ተፅዕኖቸውን እና ገቢያቸውን ከፍ ለማድረግ፣ ተለዋዋጭ የጊዜ ፕሮግራም እና የሙያ እድገት ዕድሎችን ለማግኘት የሚፈልጉ ብቁ አስተማሪዎችን እየፈለግን ነው።
መድረኩ በሌሎች ቋንቋዎች ይገኛልን?
አዎን። የእኛ መድረክ ሁለቱንም እንግሊዝኛ እና አማርኛ ይደግፋል። ሌሎች የቋንቋ አማራጮች በሂደት ላይ ናቸው። በማሰሻ ምናሌ ውስጥ ያለውን መቀየሪያ በመጠቀም ቋንቋ መቀየር ይችላሉ። እንዲሁም ቋንቋውን ለሚማሩ ተማሪዎች የኢትዮጵያ ቋንቋ ትምህርት እናቀርባለን።
ለየትኞቹ የዕድሜ ክልሎች አገልግሎት ትሰጣላችሁ?
ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ (ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ላሉ ተማሪዎች፣ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዎች ዝግጅት እናገለግላለን። ከኢትዮጵያ ተማሪዎች፣ በዓለም ዙሪያ ካሉ ዲያስፖራ ቤተሰቦች እና የተለያዩ ሥርዓተ ትምህርቶችን ከሚከተሉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ጋር እንሠራለን።
አስጠኚ ያግኙ
በነጻ የሙከራ ክፍለ ጊዜ ይጀምሩ። ፍላጎቶችዎን ከሚረዱ ብቃት ካላቸው አስተማሪዎች ጋር ይገናኙ።
